Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ከንቲባ Bowser በ15ኛው አመታዊ ኤክስፖ ላይ ለአካል ጉዳተኛ ማህበረሰብ መዋዕለ ንዋዮችን አመልክተዋል

Wednesday, October 26, 2022

(ዋሽንግተን፣ ዲሲ) – ዛሬ፣ በብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት የግንዛቤ ወር፣ ከንቲባ Muriel Bowser እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ (ODR) 15ኛውን ዓመታዊ የአካል ጉዳተኝነት ግንዛቤ ኤክስፖ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፣ይህም ውይይቱን ለአካል ጉዳተኛ ሰዎች ስለ እኩል እድሎች እና አካታች አካባቢዎች የሚደረግ ውይይትን ቅድሚያ የሚሰጥ ዝግጅት ነው። በዝግጅቱ ወቅት ከንቲባው ነዋሪዎች በዲሲ መንግስት ፕሮግራሞችን እና እድሎችን እንዲጠቀሙ እና አካል ጉዳተኛ ግለሰቦችን የሚደግፉ መዋዕለ ንዋዮችን አመልክተዋል።

ከንቲባ Bowser “የዲሲ እሴቶቻችንን ማሳደግ ማለት ለአካል ጉዳተኞች ሁሉን አቀፍ እና ፍትሃዊ የሆነች ከተማ እንዴት እንደምንገነባ ማሰብ ማለት ነው” ብለዋል። "በፕሮግራሞች እና ግብዓቶች ላይ ስራ ላይ ማዋላችንን ስንቀጥል ሰዎች ስለእነዚህ ግብዐቶች ማወቃቸውን ማረጋገጥ አለብን። እና እንደዚህ አይነት ኤክስፖዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለዚህ ነው - ስለዚህ እነዚያን ግንኙነቶች መገንባት እንችላለን እንዲሁም ሰዎች በኤጀንሲዎቻችን እና በአጋሮቻችን በኩል ስላሉት እድሎች ማወቃቸውን እናረጋግጣለን።

በከንቲባው የበጀት ዓመት 2023 በጀት፣ የዲሲ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ነዋሪዎችን የሚንከባከቡ ባለሙያዎችን ቀጥተኛ ድጋፍ ለማቆየት በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ደሞዝ በመጨመር $11.5 ሚሊዮን እንዲሁም በማሳደግ የእድገት እክል ያለባቸው ግለሰቦች የአዕምሮ እክል ካለባቸው ግለሰቦች ጋር ተመሳሳይ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ብቁነትን ለማስፋት $500,000 ያካተቱ መዋዕለ ንዋዮችን በስራ ላይ አውለዋል። እንዲሁም ከንቲባዋ ፓርኮች፣ ትምህርት ቤቶች እና የመዝናኛ ተቋማት የአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ህግን የሚያከብሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የአስተዳደሯን ቀጣይ ኢንቨስትመንት አሳይታለች።

"የከንቲባ Bowser ስልታዊ መዋዕለ ንዋዮች ነዋሪዎችን በዲስትሪክቱ ውስጥ እንዲኖሩ፣ እንዲሰሩ እና እንዲበለፅጉ ከሚረዷቸው ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጋር ለማገናኘት ቁልፍ ናቸው" ሲሉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ ዳይሬክተር፣ Mat McCullough ተናግረዋል። “ሁሉም ነዋሪዎች በከተማችን በሚያቀርበው ብልጽግና ውስጥ መሳተፍ እንዲችሉ ለውጥ ማድረግ እና እራሳችንን ተጠያቂ ማድረግ እንፈልጋለን።”

ዝግጅቱ ከበርካታ የዲስትሪክቱ የመንግስት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮው መሪ ሃሳብ “አካል ጉዳተኝነት፦ የፍትሃዊ እኩልነት አካል” የሚል ነው። ከ50 በላይ የሚሆኑ ስራዎችን የሚያሳዩ ሰዎች እንደ መኖሪያ ቤት፣ የስራ እድሎች፣ የአእምሮ ጤና እና ደህንነት በመሳሰሉ ጠቃሚ ርዕሶች ላይ መረጃ አጋርተዋል። የአካል ጉዳት ግንዛቤ ኤክስፖ በ Martin
Luther King Jr. የመታሰቢያ ቤተ መፃህፍት እስከ ዛሬ 3 pm ድረስ ይካሄዳል።

ማህበራዊ ሚዲያ:
የከንቲባ Bowser ትዊተር፦ @MayorBowser
የከንቲባ Bowser ኢንስታግራም፦ @Mayor_Bowser
የከንቲባ Bowser ፌስቡክ፦ facebook.com/MayorMurielBowser
የከንቲባ Bowser ዩቱብ፦ https://www.bit.ly/eomvideos