አገልግሎት ሰጪ እንስሳት በመጠለያ ስፍራዎች ውስጥ
በ Transcen, Inc. እና በመካከለኛው አትላንቲክ የ ADA ማዕከል የቀረበ
ይህ የ 90 ደቂቃ ክፍለ ጊዜ ነው።
ይህ ክፍለ ጊዜ የአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን ህግ እና ፍትሃዊ የመኖሪያ ቤቶች ህግ፣ ቤት የሌላቸውን፣ የአደጋ ጊዜ እና የቤት ውስጥ ጥቃት መጠለያዎችን ጨምሮ በመጠለያ ስፍራዎች ውስጥ አገልግሎት ሰጪ እንስሳትን በመቆጣጠር ላይ ያላቸውን ልዩነቶችን ዳስሷል። የኛ አቅራቢ፣ Jessica L. Hunt፣ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ ጠበቃ አማካሪ እነዚህ ህጎች ተፈጻሚ የሚሆኑባቸውን ሁኔታዎች ተናግረዋል። ብዙ ተቆጣጣሪዎች ያሏቸው ውሾችን፣ በመጠለያ ውስጥ አገልግሎት ሰጪ እንስሳትን እንዴት ማስተናገድ እንደሚችሉ እና የእንስሳት አለርጂ ያለባቸውን ግለሰቦችን ጨምሮ በመጠለያ ስፍራዎች ውስጥ ከአገልግሎት ሰጪ እንስሳት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ መመሪያ ሰጥታለች።
አገልግሎት ሰጪ እንስሳት በመጠለያ ስፍራዎች ውስጥ - የዌቢናር መዝገብ (ማስፈንጠሪያው ውጫዊ ነው)
አገልግሎት ሰጪ እንስሳት በመጠለያ ስፍራዎች ውስጥ - የዌቢናር ግልባጭ ጽሑፍ
-
ይህ ዌቢናር የቀረበው በ Blackboard Collaborate Web Conferencing መድረክ በኩል ነው።
-
የሚታይ መግለጫ ጽሑፍ በዌቢናሩ መድረክ በኩል ይቀርባል
ቀጣይነት ያለው የትምህርት እውቅና ይገኛል፦ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት
የመጀመሪያ ጊዜ የ Blackboard Collaborate Web Conferencing ስርዓት V12.6 ተጠቃሚዎች፦
ኮምፒውተርዎን ከ Blackboard Collaborate ጋር ለመጠቀም ቅድመ-ማዋቀርን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎን የመጀመሪያ ጊዜ ተጠቃሚዎች (ማስፈንጠሪያው ውጫዊ ነው) ገጽን ይጎብኙ። ማንኛውንም አስፈላጊ መላ ፍለጋ እንዲኖር ለማስቻል ከክፍለ-ጊዜው አስቀድመው እንዲያደርጉት እንመክራለን። በድርጅታዊ ፖሊሲዎችዎ ላይ በመመስረት ፋየርዎል ፋይሎችን
እንዳያወርዱ ከከለከልዎ የ IT ሰራተኞችዎን እገዛ ሊፈልጉ ይችላሉ። የዝግጅት አቀራረብን ለማየት ወደ መስመር ላይ የዌቢናር ስርዐት ለመግባት ካሰቡ የመግለጫ ፅሁፎችን ለመድረስ እና/ወይም
ጥያቄዎችን ለማስገባት የኮምፒተርዎን ስርዓት በትክክል መዋቀሩን እና የዌቢናር መድረኩን ለማግኘት አስፈላጊው ሶፍትዌር እንዳለዎት ለማረጋገጥ መመሪያዎችን መከተል አስፈላጊ ነው።
የስክሪን አንባቢ ተጠቃሚዎች፦ የ Blackboard Collaborate Web Conferencing የስክሪን አንባቢ ሶፍትዌርን የሚጠቀሙ ግለሰቦች በተደራሽነት መምሪያ (ማስፈንጠሪያው ውጫዊ ነው) ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች እና መረጃዎች ከክፍለ ጊዜው በፊት መከለስ አለባቸው።