Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ADA ርዕስ I

ODR የአሜሪካውያን አካል ጉዳተኞች ህግ - ርዕስ I የቅጥር መረጃ ሉህ

  • ማንኛውም ቀጣሪ በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ላይ ብቃት ያለው የአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ መድሎ መፈጸም የለበትም።
  • ብቃት ያለው ሰው የሥራ መደቡን ተፈላጊ ክህሎቶች፣ ልምድ፣ ትምህርት እና ሌሎች ከሥራ ጋር የተያያዙ መስፈርቶችን ያሟላል፤ እና የሥራውን አስፈላጊ ተግባራት በምክንያታዊ እገዛም ሆነ ያለ ምክንያታዊ እገዛ ማከናወን ይችላል።
  • ምክንያታዊ እገዛ በሥራ፣ በስራ አካባቢ ወይም ሥራው በተለምዶ በሚሰራበት መንገድ ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ለውጦች ወይም ማስተካከያዎች ሲሆን ብቃት ያለው አመልካች ወይም አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ አስፈላጊ ተግባራትን እንዲፈጽም ያስችለዋል።

ሰራተኛው ብዙውን ጊዜ በኤጀንሲው ውስጥ ያለው ተቆጣጣሪ ፣ HR ወይም የ ADA አስተባባሪ በመጠየቅ ምክንያታዊ የእገዛ ሂደት ይጀምራል። ጥያቄው በጽሁፍ መሆን፣ መደበኛ መሆን ወይም ማንኛውንም ልዩ ቋንቋ መጠቀም አይጠበቅበትም፣ እንዲሁም በቅጥር መጀመሪያ ላይ መጠየቅ አይጠበቅበትም። ተቆጣጣሪው ጋር በመጀመሪያ ግንኙነት ከተደረገ፣ የ ADA አስተባባሪው በሂደቱ መጀመሪያ ላይ መምጣት አለበት። በሂደቱ ውስጥ አሰሪው እና ሰራተኛው መስተጋብራዊ ውይይት ማድረግ አለባቸው እና ውሳኔው በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ መደረግ አለበት።

የምክንያታዊ እገዛዎች ዓይነቶች፦

  1. “ቴክኖሎጂ የለሽ” እገዛ ትንሽ ወይም ምንም ገንዘብ አያስከፍልም…ጊዜ፣ ድጋፍ እና ፈጠራ ብቻ (ለግለሰብ ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ)፤
  2. "ዝቅተኛ ቴክኖሎጅ" እገዛ በቴክኖሎጂ ቀላል ወይም ያልተወሳሰበ እና በአብዛኛዎቹ ቢሮዎች ውስጥ በቀላሉ የሚገኝ መስተንግዶ ነው (የተገደበ እንቅስቃሴ ያለውን ግለሰብ ለማስተናገድ ከበር እጀታ ይልቅ የበር ሉል )፤ እና
  3. “ከፍተኛ ቴክኖሎጅ” እገዛ የላቁ ወይም የተራቀቁ መሳሪያዎችን (የስክሪን ንባብ ሶፍትዌር) የሚጠቀም ማንኛውም እገዛ ነው።

ምክንያታዊ እገዛዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  1. የሥራ መልሶ ማዋቀር፤
  2. የእረፍት ጊዜ (ያልተወሰነ እረፍት አይደለም፣ ወይም በ ER ላይ ከልክ ያለፈ ችግር የሚያስከትል ከሆነ)፤
  3. የጊዜ ሰሌዳ ለውጥ፤ መሳሪያ (ቴፕ መቅረጫ፣ ስካነር፣ የድምጽ ሶፍትዌር)
  4. የሥራ ቦታ ፖሊሲ ለውጥ (በሥራ ቦታ ምግብን መፍቀድ፣ አገልግሎት ሰጪ እንስሳ መፍቀድ)፤
  5. የቁጥጥር ዘዴዎችን ማስተካከል (በተለያዩ መንገዶች ተግባራትን ማስተላለፍ፣ ተጨማሪ ስልጠና መስጠት፣ ተጨማሪ መመሪያ)፤
  6. ቤት ውስጥ መሥራት፤
  7. የሥራ አሰልጣኝ አቅርቦት።

ምክንያታዊ መስተንግዶዎች የሚከተሉትን አያካትቱም፦

  1. የመድሃኒት ክትትል፤
  2. የምርት ደረጃን ዝቅ ማድረግ፤
  3. የግል መጠቀሚያ ዕቃዎች አቅርቦት (የመስሚያ መርጃዎች፣ ተሽከርካሪ ወንበሮች)፤
  4. የተቆጣጣሪ ለውጥ።

አሰሪው ሰራተኛው እገዛ እንዲቀበል ማስገደድ አይችልም።

ስለ ምክንያታዊ እገዛ እና ስለ ሂደቱ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የሚከተሉትን ይመልከቱ፡-  “አካል ጉዳተኞችን ለማገዝ የሚያገለግል የዲሲ መንግስት መመሪያ”.