Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

በተደራሽ ውይይቶች እና ስብሰባዎች ላይ የዲሲ መንግስት መመሪያ

መግቢያ

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚደረጉ ውይይቶች እና ስብሰባዎች መረጃ ለመለዋወጥ፣ ስልቶችን ለማዘጋጀት፣ ለጋራ ዓላማዎች ለመስራት እና በአለም አቀፍ፣ በብሄራዊ እና በአካባቢያዊ ደረጃዎች ስኬቶችን ለማክበር ሰዎችን አንድ ላይ ያሰባስባሉ። የእነዚህ ዝግጅቶች ስኬት ደረጃ የሚወሰነው በታዳሚዎች ተሳትፎ ብቻ ነው። ዝግጅቶችን ለማቀድ ከተሰጠው ጊዜ፣ ጥረት እና ግብአት አንጻር ሁሉም ታዳሚዎች ሙሉ በሙሉ መሳተፍ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ጥሩ የንግድ ስራ ነው።

ውይይቶች እና ስብሰባዎች ሲዘጋጁ የአካል ጉዳተኞች መስተንግዶ እና የማካተት ፍላጎቶች ብዙ ጊዜ ችላ ይባላሉ።
 
በተደራሽ ውይይቶች እና ስብሰባዎች ላይ ያለው የዲሲ መንግስት መመሪያ በውይይቶች እና ስብሰባዎች ላይ የአካል ጉዳተኞችን ሙሉ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ለዲሲ የመንግስት ኤጀንሲዎች እና ባለስልጣኖችን ተግባራዊ ጠቃሚ ምክሮችን እና ምክረ ሃሳቦችን ይሰጣል።
 
ይህ መመሪያ የተዘጋጀው እና የተስፋፋው በ ODR ሲሆን ዓላማውም በእቅድ ዝግጅቱ ሂደት ውስጥ ለማገዝ እና የተሻለውን የተደራሽነት ደረጃ ለማንፀባረቅ ነው። አንዳንድ ተቋማት በዚህ ሰነድ ውስጥ የተዘረዘሩትን ሁሉንም መስፈርቶች ላያሟሉ ይችላሉ:: ኤጀንሲው ሊሆን በሚችል ቦታ ስላለው የተደራሽነት ደረጃ ጥርጣሬ ካደረበት፣ የኤጀንሲው ኃላፊዎች ODR ን ማማከር አለባቸው።
 
መረጃ እና እርዳታ ለማግኘት፣ እባክዎን የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮን ያነጋግሩ።
 
ድረ ገጽ፦odr.dc.gov
የ ODR ዋና ቁጥር፦ (202) 724-5055
TTY፦ (202) 727-3363   
ፋክስ፦ (202) 727-9484
ቦታ፡ 441 4th Street NW
                Suite 729 North
                Washington, DC 20001