Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

አካል ጉዳተኞች

አካል ጉዳተኞች እነማን ናቸው?

ADA ሶስት የግለሰቦችን ምድቦች በአካል ጉዳታቸው ላይ በመመስረት ከሚፈጸም አድልዎ ይጠብቃል፦

  • እንደ ዓይነ ስውርነት፣ መስማት አለመቻል፣ ሽባ መሆን (ሴሬብራል ፓልሲ)፣ ካንሰር፣ የልብ ህመም፣ የአእምሮ እክል፣ የአእምሮ ጉዳት፣ የስሜት ወይም የአእምሮ ህመም እና ልዩ የመማር እክሎችን የመሳሰሉ ህመሞችን ጨምሮ - በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ዋና ዋና የህይወት እንቅስቃሴዎችን በእጅጉ የሚገደቡ የአካል ወይም የአዕምሮ እክል ያለባቸው ግለሰቦች።

  • ከአእምሮ ወይም ከስሜት ህመም፣ ከዕፅ ሱስ፣ ከልብ ህመም ወይም ከካንሰር ያገገሙ ሰዎችን ጨምሮ ዋና ዋና የህይወት እንቅስቃሴዎችን በእጅጉ የሚገድቡ የአካል ወይም የአዕምሮ እክል መዝገብ ያላቸው ግለሰቦች።

  • ያለባቸው የአካል ጉዳት ምንም ይሁን ምን እንደዚህ አይነት የአካል ጉዳት አለባቸው ተብለው የሚታሰቡ ግለሰቦች። ምንም ዓይነት የአሠራር እክል የሌለበት፣ ነገር ግን ሰዎች ግለሰቡን እንደ አካል ጉዳተኛ አድርገው ሊመለከቱት የሚችሉት ከመጠን በላይ ወፍራም የሆነ ወይም በአደጋ ምክንያት ጠባሳ ሆኖ የቀረበት አንድ ሰው የተለመዱ ምሳሌዎች ናቸው።

በተጨማሪም ADA ሰዎችን ከአካል ጉዳተኛ ሰው ጋር ባላቸው ህብረት ከሚደርስባቸው መድልዎ ወይም የ ADA መብቶችን በማረጋገጣቸው ከሚደርስባቸው የበቀል እርምጃዎች ይጠብቃል።