Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

የኤጀንሲ ADA አስተባባሪዎች

ODR አካል ጉዳተኞች ስላላቸው መብቶች መረጃን መስጠት እና በአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ህግ (ADA) መስፈርቶች እና ሌሎች አካል ጉዳተኞችን በሚመለከቱ ህጎች ላይ የቴክኒክ ድጋፍ እና መመሪያ ማቅረብ ይችላል።
እንዲሁም ADA ስር ያልዎት መብቶች እንደተጣሱ ከተሰማዎት የእኛ ቢሮ መደበኛ ቅሬታ እንዲያቀርቡ ሊረዳዎት ይችላል።

  • ቅሬታ እንዴት እንደያቀርቡ የሚያሳይ ቪዲዮ
  • ድጋፍ ይጠይቁ ወይም ቅሬታ ያስገቡ - የመስመር ላይ ቅጽ
  • ADA ቅሬታዎች - የድጋፍ ቅጽ - ሊታተም የሚችል ስሪት [PDF]

እባክዎ ይህን ቅጽ ከሚከተሉት ለአንዱ ያቅርቡ፦

ምክንያታዊ እርዳታዎች ከፈለጉ፣ እባክዎ የኤጀንሲውን ADA አስተባባሪ ያነጋግሩ ወይም ይህንን ቅጽ ይሙሉ።

እባክዎን የዲስትሪክት የእኩል የስራ ስምሪት መኮንንን ለማግኘት የዲሲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮን ያነጋግሩ።

https://ohr.dc.gov/page/EEOcounselors

 

የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት

ድንገተኛ ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ ሊከሰቱ ይችላሉ። እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ይወቁ፡-
የሚከተሉትን ይወቁ፦ ስለ አደጋዎች እና ድንገተኛ አደጋዎች ይወቁ

እቅድ ያውጡ፦ የሚያስፈልግዎትን ነገር ያስቡ

መሳሪያ ያደራጁ፦ አቅርቦቶችዎን ይሰብስቡ

ለበለጠ መረጃ ready.dc.gov ይጎብኙ ወይም ወደ 311 ይደውሉ።
አዲሱን መመሪያችንን ይመልከቱ፦

ለአደጋ ጊዜ እቅድ ለማውጣት የዲስትሪክት ነዋሪዎች መመሪያ እድሜ፣ ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ የኑሮ ሁኔታ ወዘተ ሳይለይ በማንኛውም ሰው ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። መመሪያው ከድንገተኛ አደጋ በፊት የዝግጅት እቅድ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ንድፎችን እና የእቅድ ሰነዶችን ያቀርባል። የመጠለያ ቦታን ወይም
መመሪያ ሲሰጥ፣ ቤት ለቀው ለመውጣት እና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት መሳሪያ ማደራጀትን የሚያካትት እቅድ እንዴት እንደሚዘጋጅ በዝርዝር ያቀርባል። መመሪያውን ይመልከቱ፣ የዲስትሪክት ነዋሪዎች

ለአደጋ ጊዜ እቅድ ለማውጣት የሚረዳ መመሪያ Ready.DC.gov ላይም ይገኛል።
ዓባሪ(ዎች)

ለዲስትሪክት ነዋሪዎች ለድንገተኛ አደጋ እቅድ ለማውጣት የሚረዳ መመሪያ -1.9 MB (pdf)

https://ready.dc.gov/
https://odr.dc.gov/sites/default/files/dc/sites/odr/ODR%20Guidebook-DIGITAL-FINAL-20190131.pdf
https://odr.dc.gov/sites/default/files/dc/sites/odr/service_content/attachments/ODR%20Guidebook-DIGITAL-FINAL-20190131.pdf

አገልግሎቶች

  • ADA ስልጠና- ለዲሲ ኤጀንሲዎች ADA እና ሌሎች የአካል ጉዳት መብቶች ህጎች እና ደንቦች ስልጠና እንሰጣለን።
  • የኤጀንሲ ADA አስተባባሪዎች- ODR ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች መረጃ፣ መመሪያ እና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል።
  • የብሬይል (የአይነስውራን ስርዐተ ጽህፈት) አገልግሎቶች የትርጉም ፕሮግራም- የዲሲ የመንግስት ሰነዶች በተጠየቁ ጊዜ በብሬይል ቋንቋ ሊቀርቡ ይችላሉ።
  • የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት- ድንገተኛ ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ ሊከሰቱ ይችላሉ። እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ይወቁ።
  • መመሪያ- ለድርጅትዎ ፕሮግራሞች፣ ጥቅማጥቅሞች እና አገልግሎቶች እኩል ተደራሽነት እንዲያቀርቡ ልንረዳዎ እንችላለን።
  • የምልክት ቋንቋ አገልግሎቶች- የከንቲባው መስማት የተሳናቸው፣ መስማት እና ማየት ለተሳናቸው፣ መስማት የሚቸገሩ ሰዎች ቢሮ ለአብዛኛዎቹ የዲሲ ኤጀንሲ ስብሰባዎች እና ህዝባዊ ተግባራት የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ አገልግሎት ይሰጣል።
  • በአካል ጉዳተኝነት መብቶች ቢሮ የቪዲዮ ስልጠናዎች- የዲሲ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ (ODR) ሁሉም የዲስትሪክት መንግስት ሰራተኞች በአጭር እንደአስፈላጊነቱ በሚቀርቡ የሥልጠና ተከታታዮች

https://odr.dc.gov/service/ada-training
https://odr.dc.gov/service/agency-ada-coordinators
https://odr.dc.gov/service/Braille-Services
https://odr.dc.gov/Emergency-Preparedness
https://odr.dc.gov/service/guidance
https://odr.dc.gov/service/sign-language-services

 

መብቶችዎን ይወቁ

የአሜሪካውያን የአካል ጉዳተኞች ህግ (ADA) መኖር፣ መስራት እና በማህበረሰብ ውስጥ ለሚከተሉት በእኩል ተደራሽነት መሳተፍ እንደሚችሉ በማረጋገጥ አካል ጉዳት እንዳለበት ብቁ ግለሰብ መብቶችዎን ይጠብቃል፡-

  • የቅጥር እድሎች
  • የመንግስት ፕሮግራሞች፣ ጥቅማጥቅሞች እና አገልግሎቶች
  • ውጤታማ ግንኙነት
  • ትራንስፖርት
  • የመንግስት ሕንፃዎች እና ተቋማት

ስለ መብቶችዎ የበለጠ ለማወቅ፣ ከዚህ በታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች ጠቅ ያድርጉ ወይም ስለ ODR ትር ስር
የሰራተኛ ማውጫችንን ተጠቅመው የአካል ጉዳተኞች መብቶችን ቢሮን ያነጋግሩ።

 

Olmstead የማህበረሰብ ውህደት እቅድ - ዲሲ አንድ ማህበረሰብ ለሁሉም

በ1990 የአሜሪካ የአካል ጉዳተኞች ህግ (ADA) በህግ ተፈረመ፣ የግዛት እና የአካባቢ መንግስታት አካል ጉዳተኞች በመንግስት አገልግሎቶች፣ ፕሮግራሞች ወይም ተግባራት እንዳይሳተፉ ወይም ጥቅማጥቅሞችን እንዳይቀበሉ በማግለል አድልዎ እንዳይፈጽሙ ይከለክላል። ADA የግዛት እና የአካባቢ መንግስታት ብቁ ለሆኑ አካል ጉዳተኞች ፍላጎቶች በደንብ በተቀናጀ ሁኔታ ተገቢ የሆኑ አገልግሎቶችን፣ ፕሮግራሞችን እና እንቅስቃሴዎችን እንዲሰጡ ያስገድዳል። ይህ ብዙ ጊዜ የ ADA “የውህደት ህግ” ይባላል።
ይህንን የውህደት ህግ ለመቃወም የመጀመሪያው ጉዳይ የነበረው Olmstead v. L.C. ሲሆን፣ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አካል ጉዳተኞች ከተቋማዊ ቅንብር ይልቅ በማህበረሰቡ ውስጥ የመኖር እና እንክብካቤ የማግኘት መብት እንዳላቸው ደንግጓል። በዚህ የ1999 ውሳኔ፣ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የ ADA የውህደት ህግ ተገዢነትን ለማሳየት ግዛቶች “ሁሉን አቀፍ፣ ውጤታማ የስራ እቅድ” ሊኖራቸው እንደሚችል አመልክቷል። እነዚህ እቅዶች ብዙውን ጊዜ “የ Olmstead ዕቅዶች” ይባላሉ።
በ Olmstead ስር፣ ግዛቶች በተወሰነ ገደብ ውስጥ ለአካል ጉዳተኞች በተቀናጁ ቅንብሮች ውስጥ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚችሉ ማሳየት አለባቸው፦

  • ግለሰቡ ማህበረሰብን ማዕከል ያደረጉ አገልግሎቶችን መፈለግ አለበት፤
  • የግለሰቡ ህክምና ቡድን ማህበረሰብን ማዕከል ያደረጉ አገልግሎቶች ተገቢ እንደሆኑ ማጤን ይኖርበታል።
  • እና የግዛት መርጃዎችን እና ሌሎች የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎቶች ግምት ውስጥ በማስገባት ማህበረሰቡን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ለማስተናገድ ምክንያታዊ መሆን አለበት።

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ Olmstead እቅድ

 

Olmstead የስራ ቡድን ODR እና ሌሎች አካል ጉዳተኞችን በሚያገለግሉ ኤጀንሲዎች ምክር እና ምክረ ሃሳቦች ተዘጋጅቷል። ቡድኑ የአካል ጉዳተኞች እና የአካል ጉዳተኞች ጠበቆችን ጨምሮ ከዲስትሪክቱ ኤጀንሲዎች የተውጣጡ ተወካዮች እና የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ነው። የስራ ቡድኑ በጋራ፣ እቅዱ ምን መምሰል እንዳለበት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ምን መሆን እንዳለባቸው ለዲስትሪክት መንግስት ኤጀንሲዎች ይመክራል። የዲስትሪክቱ 2021-2024 Olmsteadእቅድ በመኖሪያ ቤት፣ በጤና እንክብካቤ እና በስራ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ላይ ያተኩራል።


ዕቅዱ የሚከተሉት ሦስት ዓላማዎች ይኖሩታል፦


• የዲሲ መንግስት ድጋፎችን እና አገልግሎቶችን በመጠቀም ከረጅም ጊዜ እንክብካቤ ወደ ማህበረሰቡ የሚሸጋገሩ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎችን ብዛት ይከታተላል።
• ሰዎች ከረጅም ጊዜ እንክብካቤ ወደ ማህበረሰቡ እንዲሸጋገሩ የሚረዱ የዲስትሪክቱን መንግስት ፕሮግራሞችን እና ፖሊሲዎችን ያሳያል።
• በሽግግር ላይ ያለ ሰው በእነዚህ ሶስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ስር አገልግሎቶችን ስለ ለማሳወቅ እንደ መመሪያ ሆኖ ያገለግላል።
ስለ

ስለ ODR

የተልዕኮ መግለጫ

  • የዲሲ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ (ODR) ተልእኮ በዲስትሪኢክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሚተዳደሩ ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ፕሮግራሞች፣ አገልግሎቶች፣ ጥቅማጥቅሞች፣ ተግባራት እና ተቋማት በአካል ጉዳተኛ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ተደራሽ እና ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው። ODR አካል ጉዳተኞችን ለማካተት፣ ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶች ለመስጠት እና የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። ODR በአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን ህግ (ADA) እና ሌሎች የአካል ጉዳተኝነት መብቶች ህጎች መሰረት የከተማዋን ግዴታዎች አፈፃፀም እንዲቆጣጠር በዲሲ ምክር ቤት እና በከንቲባዋ ተሹሟል።

ODR አገልግሎቶች

  • የመድልዎ ቅሬታዎችን መመርመር።
  • ለዲስትሪክት ኤጀንሲዎች የ ADA ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ።
  • የኤጀንሲዎችን የ ADA ዕቅዶች በመከታተል በዲስትሪክቱ መንግሥት ውስጥ የ ADA ተገዢነትን መቆጣጠር።
  • በኤጀንሲዎች ከተሾመ የ ADA አስተባባሪ ጋር መስራት።
  • Olmstead (የማህበረሰብ ውህደት) እቅድ ማውጣት::
  • የዲስትሪክት አካል ጉዳተኛ ሰዎችን ተደራሽነት ለማሻሻል የፖሊሲ እና የበጀት ምክረ ሃሳቦች።

ODR ለዲሲ የዴቨሎምንታል ዲሰብሊቲ ካውንስል (DDC) የተሾመ የግዛት ኤጀንሲ (DSA) ሆኖ ያገለግላል፣ ይህ ማለት የ DDC ሰራተኞች በ ODR የህዝብ ስም ዝርዝር ውስጥ የቀረቡ ሲሆን ODR የ DDC በጀት እና ከፕሮግራም ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ለከንቲባዋ የማቅረብ ሃላፊነት ተጥሎበታል።